Sign Up?

User name ከሚለው ላይ የሚያስታውሱት የፈለጉትን ስም መስጠት ይችላሉ፡፡ full name ከሚለው ላይ ሙሉ ስምዎትን ያስገቡ፡፡ email ከሚለው ላይ ኢሜልዎትን ያስገቡ፡፡ እንዲሁም password ከሚለው ላይ ፓስወርድዎትን ያስገቡ፡፡ ሲጨርሱ Partner User (Used for register vehicles and booking services) የሚለውን ተጭነው እንዲሁም I have read and accept the terms and conditions ከሚለው ላይ ከመኪና ኪራይ ጋር በአጋርነት ለመሥራት መስማማትዎን በመግለጽ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ ቀጣይ የሚሆነው የመኪና ኪራይ ተሸከርካሪ ኪራይ ሽያጭ ክፍል የአጋርነት ጥያቄውን አረጋግጠው ቀጣይ ማድረግ ያለብዎትን ይነግሩዎታል፡፡ እግዛ ከፈለጉ እባክዎት አሁኑኑ ይደውሉልን፡፡ በደስታ ልናስተናግድዎ ዝግጁ ነን፡፡

ተከራይቶ የነበር ተሽከርካሪ ስታቲስቲክስ/ Vehicle Statistics ?

አንድ ቁጥር ላይ Dashboard የሚለውን ሲጫኑት 2 ቁጥርን ያሳየዎታል፡፡ ሁለት ቁጥርን ሲጫኑት Vehicle Statistics የሚል ገጽ ይከፍትልዎታል፡፡ NET EARNING THIS MONTH የሚለው ላይ በዚህ ወር የተጣራ የሚከፈልዎት ክፍያ የሚያሳይ ሲሆን YOUR BALANCE የሚለው ላይ የሚመለከቱት ቁጥር ተሸከርካሪዎ ተከራይቶ አጠቃለይ የሚከፈለዎን ክፍያ ሲሆን NET EARNING ሚለው ላይ የሚያዩት ቁጥር ደግሞ ለእርስዎ የሚከፈልዎት የተጣራ ክፍያን ይሆናል፡፡

ስምና አድራሻን ለማስገባት/ settings ?

ሴቲነግ የሚለውን ሲጫኑት Account Setting የሚል ገጽ ይከፍትልዎታል፡፡ ከዚህ ገጽ ላይ የግል ማህደረዎትን ከፈለጉ በሚፈልጉት ሁኔታ የሚያስተዳድሩበትን ገጽ የሚያገኙበት ነው፡፡

የተከራየ ተሽከርካሪ ታሪክ/ booking history?

አጋሮች (Partners) መኪና ኪራይ ተሸከርካሪ መከራያያ ድህረ-ገጽ ላይ ሊከራዩ ዝግጁ የሆኑትን የሌላን ግለሰብ/ድርጅት ተሽከርካሪ ለመከራየት ድህረ-ገጹ ላይ የፈለጉትን ተሸከርካሪ መርጠው ተሸከርካሪው ያለበትን ፎቶ ሲጫኑት መከራየት የፈለጉትን ተሸከርካሪ መመዝገቢያ ቅጽ ሞልተው ከላኩ በኋላ መረጃውን የሚያገኙት Booking History ሚለው ገጽ ላይ ነው፡፡ በሌላ በኩል ዳሽቦርዱ ላይ My vehicle ከዚያም add new vehicle ከሚለው ወረድ ብሎ add booking vehicle የሚለውን ከፍተው መከራየት ስለፈለጉት ተሽከርካሪ ፎርሙን ሞልተው ከላኩ በኋላ መረጃውን የሚያገኙት Booking History የሚለው ገጽ ውስጥ ነው፡፡

መከራየት የተመኙት ተሸከርካሪ / wish list?

ከመኪና ኪራይ ድህረ-ገጽ ላይ ከሚገኙት ተሸከርካሪዎች መካከል የሚፈልጉትን ተሸከርካሪ ከፍተው ከተሽከርካሪው ፎቶ ከፍ ብሎ በነጭ ቀለም የልብ ቅርጽ ያላት ምስል ሲጫኑት ያን ተሸከርካሪ Wishlist ገጽ ውስጥ ያስቀምጥልዎታል፡፡ አላማውም መከራየት የፈለጉትን ተሸከርካሪ ቀደም ሲል በተገለጸው ሁኔታ እየመረጡ በፈለጉት ጊዜ በድጋሚ የሚከራዩትን ተሸከርካሪ መፈለግ ሳያስፈልገዎ Wish list ውስጥ በመግባት ቀሪ መመሪያዎችን ተከትለው የሚፈልጉትን ተሸከርካሪ መከራየት የሚያስችልዎት ክፍል ነው፡፡

ማስታወቂያ/ inbox notification?

የመኪና ኪራይ የተሸከርካሪ ኪራይ ሽያጭ ወይም የቴክኒካል ክፍል መልክት ከላከልዎት የሚያገኙት Inbox Notification ውስጥ ሲሆን ይህ ገጽ እርስዎም ወደ መኪና ኪራይ የተሸከርካሪ ኪራይ ሽያጭ ወይም የቴክኒካል ክፍል መልክት መላክ የሚያስችልዎት ገጽ ነው፡፡

የተሸከርካሪ ኪራይ ብር ለማውጣት/ Withdrawal ?

1 ቁጥር ላይ withdrawal ሲጫኑት ሙሉ ገጹን ይከፍትልዎታል፡፡ 2 ቁጥር ላይ your balance ከሚለው ላይ የሚመለከቱት ቁጥር የሚያሳየው ተሸከርካሪዎት ተከራይቶ የሚከፈለዎት የተጣራ ክፍያ የሚያሳይ ሲሆን Money Availability የሚለው ላይ የሚመለከቱት ለእርስዎ የሚከፈለዎትን የተጣራ ክፍያ ሳይቀነስ ተከራዮች የከፈሉትን ጠቅላላ ክፍያ የሚያሳይዎት ነው፡፡ 4 ቁጥር ላይ የሚመለከቱት ፎርም መኪና ኪራይ እንዲከፍልዎት የሚፈልጉትን የክፍያ መጠን የሚያስገቡበት ሲሆን 5 ቁጥር ላይ ሙሉ የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን እና የሒሳብ ቁጥሩ ባለቤት እና የባንኩን ስም አስገብተው submit ሲሉት የመኪና ኪራይ ሒሳብ ክፍል መረጃውን መርምረው ክፍያውን በባንክ እንዲላክልዎት የሚያስችልዎት ነው፡፡  6 ቁጥር ተሸከርካሪዎን አከራይተው ስለተከፈልዎት ክፍያ ታሪክ የሚያገኙበት ነው፡፡

የተመዘገበ ተሸከርካሪ ለማየት/ለማረም/ my vehicles ?

1 ቁጥር የሚያሳይዎት Vehicle ወይም my vehicle የሚለውን ሲከፍቱት እንዲከራይልዎት ያስገቡትን የተሸከርካሪዎን ሙሉ መረጃ ያሳይዎታል፡፡ 2 ቁጥር የሚያሳይዎት እንዲከራይልዎት ስላስገቡት ተሽከርካሪ መረጃ ማስተካከል/ማዘመን የሚችሉበትን ቁልፎች የሚያሳይ ነው፡፡ 3 ቁጥር የሚያሳይዎት ደግሞ ሌላ ተሸከርካሪ መጨመር ቢፈልጉ እንዲችሁ የሚያደርገዎትን ቁልፍ ነው፡፡

የሚከራይ ተሸከርካሪ ለማስገባት/Add car?

Add new vehicle የሚለው ክፍል እንዲከራይልዎ ስለፈለጉት ተሸከርካሪ መመሪያውን ተከትለው ሙሉ መረጃ የሚያስቀምጡበት ክፍል ነው፡፡ ይህ ክፍል በጥንቃቄ የሚሞላ ሲሆን መመሪያዎችን እና ተሸከርካሪዎ ስለሚከራይበት አጠቃለይ ዋጋ፣ ስለተሸከርካሪዎ ይዞታ፣ ፎቶ (ከፊት/ ከኋላ/ ከጎን እና ከውስጥ 4 ፎቶ ያንሱ) አድራሻ ወዘተ መረጃ የሚያስቀምጡበት ክፍል ነው፡፡

ተጨማሪየሚከራይ ተሸከርካሪ ማስገባት/ Add booking Vehicle?

Add booking vehicle የሚለውን ቁልፍ ሲከፍቱት ሙሉ ገጹን ይከፍትልዎታል፡፡ 1 ቁጥር ከሚያሳይዎት በታች ተሸከርካሪ መከራየት የፈለገውን ግለሰብ ወይም ድርጅት ሙሉ ስም እና አድራሻ የሚመዘግቡበት ሲሆን 2 ጥር በታች የሚገኘው ፎርም ላይ ስለሚከራየው ተሸከርካሪ መረጃ የምናስገባበት ፎርም ነው፡፡ ከዚህ ገጽ ላይ ስለሚከራዩት ተሸከርካሪ መረጃ ማስገባት የሚቻለው ተሸከርካሪው ከመኪና ኪራይ ድህረ-ገጽ ላይ መረጃው ተጨምሮ ከሆነ ብቻ ነው፡፡

ትራንፖርት አገልግሎት/ surface transport ?

Add booking vehicle transfer የሚለውን ቁፍል ሲከፍቱት ሙሉ ገጹን ይከፍትልዎታል፡፡ ከዚያም 1 ቁጥር ላይ የተጓዥን ሙሉ ስምና አድራሻ አስገብተው 2 ቁጥር ላይ ተጓዦችን ከቦታ ቦታ ለአንድ ጉዞ የትራንፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መኪኖችን ለመከራየት ወይም የአውቶቡስ አገልግሎት የሚሰጡ መኪኖችን ዝርዝር ስለሚከራዩበት ቀን ሰዓት ወዘተ ሞልተው ለመኪና ኪራይ ትራንስፖርት አገልግሎት ሽያጭ ክፍል እንዲልኩ የሚያስችልዎት ቅጽ ነው፡፡

ለትራንስፖርት ወይም ለኪራይ የመዘገቧቸው ተሽከርካሪዎች / vehicle bookings?

Vehicle bookings የሚለውን ሲከፍቱት ገጹን ይከፍትልዎታል፡፡ 1 ቁጥር የሚያሳየዎት ላይ car normal የሚለውን ሲጫኑት ቀደም ሲል የተከራዩአቸውን ወይም ሊከራዩአቸው የጠየቋቸውን ተሸከርካሪዎች መረጃ የሚያገኙበት ሲሆን car transfer የሚለውን ሲከፍቱት ለአንድ ጉዞ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥዎት ጠይቀው የነበረውን ተሸከርካሪ መረጃ የሚያገኙበት ክፍል ነው፡፡

የአጋሮች መረጃ/verification

Verification የሚለውን ሲከፍቱት ቅጹን/ፎርሙን ይከፍትልዎታል፡፡ 1 ቁጥር በታች ላይ የሥራ/የቀበሌ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ላይ የተጻፈ ሙሉ ስም የመታወቂያ ወይም የፓስፖርትዎን ወይም የመንጃ ፈቃድ ቁጥር እና የትውልድ ቀን ይሙሉ፡፡ 2 ቁጥር የሚያሳየዎት በታች ያለውን ቅጽ መሙላትም መተውም ይችላሉ፡፡ ድርጅት ካለዎት ግን በመጠየቁ መሰረት ቅጹን ይሙሉ፡፡ ከታች የማኅበራዊ መገናኛ መንገዶችንም ተጠቅመው መመዝገብ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ከታች የፌስቡክ አርማ የሚያሳይዎት ላይ ሲጫኑት ፌስቡክ ላይ የተመዘገቡበትን ስምዎን ወዘተ በራሱ ይመዘግብልዎታል፡፡ በኋላ Submit የሚለውን ሲጫኑት መረጃውን ወደ ድህረ-ገጹ አስተዳዳሪዎች ይልክልዎታል፡፡ አስተዳዳሪዎችም መረጃውን መርምረው ሲያረጋግጡ ከላይ በትልቁ የተጻፈ verification ከሚለው ጽሑፍ ፊት ለፊት በአረንጓዴ ቀለም የተጻፈ verified የሚል መልክት ይመለከታሉ፡፡

የአጋሮች የውል ስምምነት /partners-agreement?

1 ቁጥር የሚያሳይዎት ላይ verification የሚለውን ሲከፍቱት ገጹን ይከፍቱልዎታል፡፡ 2 ቁጥር ላይ click here የሚለውን ሲጫኑት አሳሹ ወይም ብሮወዘርዎ (browser) በአዲስ ገጽ ከመኪና ኪራይ ጋር በትብብር ለመሥራት ስለመስማማትዎ ውሉን አንብበው ከታች ስምዎን እና አድራሻዎን አስገብተው ፈርመው ሲጨርሱ submit የሚለውን ሲጫኑት በጋራ ለመሥራት ስለመስማማትዎ የሚያስረዳውን የውል ስምምነት ወደ መኪና ኪራይ አስተዳደር ይልክልዎታል፡፡