እንኳን ወደ መኪና ኪራይ ዶትኮም  የሌሎች ግለሰቦችን ወይም ድርጅቶችን ተሸከርካሪ መመዝገቢያ ቅጽ በደህና መጡ!

 

መኪና ኪራይ ዶትኮም የግንባታ ማሽኖችን እና የግብርና መሳሪያዎችን (ትራክተር፣ ኮምባይነር ወዘተ) ጨምሮ ማንኛውንም ተሸከርካሪ ማከራያ እና መከራያ ፕላትፎርም ነው፡፡ እባክዎ የሚመዘግቡትን ተሸከርካሪ ከታች ቅጹ ላይ ከመመዝገብዎ በፊት ቀጥሎ የሚገኙትን መመሪያዎች በጥንቃቄ ያንብቡ፡፡

የሌሎች ግለሰቦችን ወይም ድርጅቶችን ተሸከርካሪ የመመዝገብ አላማ ?
መኪና ኪራይ ዶትኮም ኢትዮጵያ ውስጥ ተሸከርካሪ በተመጣጣኝ ዋጋ በቀላሉ ማከራየትና መከራየት እንዲቻል ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር አላመው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን የሌሎች ግለሰቦችን ወይም ድርጅቶችን ተሸከርካሪዎች ከታች ከሚገኘውን ቅጽ የመሙላት መሰረታዊ አላማ የሚከራዩ ተሸከርካሪዎችን በብዛትና በተመጣጣኝ የኪራይ ዋጋ ለተከራይ ለማቅረብ እና ለኪራይ ዝግጁ የሆኑ ተሸከርካሪዎችን መዝግበው ለሚልኩልን ግለሰቦች ጊዜአዊ የሥራ እድል ለመፍጠር ነው፡፡ ይህን ቅጽ እንዲሞሉ የሚፈቀድላቸው ከተሸከርካሪ ባለንብረቶች ውጭ የሆኑ ግለሰቦች ብቻ ናቸው፡፡
ከቅጹ ላይ እንዲመዘገቡ የተፈቀዱ የተሸከርካሪ ዓይነቶች?
ከዚህ ቀጽ ላይ እንዲመዘገቡ የሚፈቀደው ፒካፕ እና ላንድ ክሮዘር መኪኖችን ብቻ ሲሆን ከተጠቀሱት መኪኖች ውጭ የሆኑ ለኪራይ ዝግጁ የሆኑ መኪኖችን ለሚያከራዩ ባለንብረቶች ይህን https://mekinakiray.com/list-your-car/ የሚለውን ማስፈንጠሪያ ኮፒ አድርገው በፈለጉት ማሰሻ (Browser) ከፍተው ቀጣይ መመሪያዎችን ተከትለው አጋር (Partner) የሚለወውን በመምረጥ አካውንት በመክፈት እንድናከራየው ስለተፈለገው ተሸከርካሪ መረጃ ማስገባት ይቻላል፡፡ በመኪና ኪራይ ዶትኮም የማይከራይ ተሽከርካሪ የለም፡፡ ለበለጠ መረጃ ይህን https://mekinakiray.com/partner-rent-info/ የሚለውን ማስፈንጠሪያ ኮፒ አድርገው በፈለጉት ማሰሻ (Browser) ከፍተው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ቅጹን ለመሙላት በምሳሌነት ስለቀረቡ የተሸከርካሪ ሰሌዳ ቁጥሮች?
አንድ ተሸከርካሪ ለምሳሌ ሰሌዳው A.A03-05417 ነው ብንል ከቅጹ ላይ በቀጥታ A.A03-05417 እንዲሁም ለምሳሌ ሰሌዳ ቁጥሩ A.A03-A05417 ወይም A.A03-B05417 ወይም A.A03-C05417 የሆነ ተሸከርካሪ በቀረበው ምሳሌነት መሰረት መመዝገብ ይቻላል፡፡ ቅጹ ላይ ሰሌዳው ሲመዘገብ የእንግሊዝኛ ፊደላት (spelling)፣ ቁጥር፣ ጭረት (-) እና አንድ ነጥብ (.) ውጭ የሆኑ አማርኛ ፊደላትን ጨምሮ ማንኛውንም ምልክት መጠቀም እንዲሁም በእንግሊዝኛ ፊደላቱ፣ በነጥቡ፣ በቁጥሩ እና በጭረቱ መካከል ክፍተት መፍጠር አይቻልም፡፡ የሚመዘገበው ተሸከርካሪ ከዚህ ቀደም በመመሪያው መሰረት ተመዝግቦ ከነበር ሲስተሙ ‹‹ተሽከርካሪው ከዚህ ቀደም ተመዝግቧል፡፡ ሌላ ተሸከርካሪ ይመዝግቡ›› የሚል መልስ ይሰጥዎታል፡፡
ተሸከርካሪው ከዚህ ቀደም ተመዝግቦ መሆን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ ?
ቅጹ ከመሙላትዎ በፊት የሚመዘግቡት ተሸከርካሪ ከዚህ ቀደም ተመዝግቦ መሆን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ ከታች ‹‹ይህን ቅጽ የሞላው ሰው ሙሉ ስም›› ከሚለው ከፍ ብሎ ከሚገኘው ቅጽ ላይ ከላይ በምሳሌነት በተቀመጡት ሰሌዳ ቁጥሮች መሰረት ሰሌዳውን አስተካክለው Submit የሚለውን ይጫኑት፡፡ ቀጥለው ‹‹የተሸከርካሪውን ሰሌዳ ያስገቡ) ከሚለው ቅጽ ላይ ሲስተሙ የመለሰልዎትን መልስ ያንብቡ፡፡ ሲስተሙ ‹‹ተሽከርካሪው ከዚህ ቀደም ተመዝግቧል፡፡ ሌላ ተሸከርካሪ ይመዝግቡ›› ከአላለዎት ተሸከርካሪው ከዚህ ቀደም አልተመዘገበም ማለት ስለሆነ ቀሪዎችን ቅጾች (ፎርሞች) በጥንቃቄ ሞልተው ከታች Submit የሚለውን መልሰው ተጭነው ይላኩልን፡፡
ስለ ክፍያ ሁኔታ ?
መዝጋቢዎች ከላይ በተቀመጠው ምሳሌነት በትክክል መዝግበው ሲልኩልን ተሸከርካሪዎቹ የተሠሩበትን ዘመን መሰረት አድርገን የመኪና ኪራይ ዶትኮም ሕጋዊ ተጠሪ በሆነው በታንኳ አስጎብኝና የጉዞ ወኪል በኩል ክፍያዎን እንከፍለወታለን፡፡ ፒክ አፕ (Pick Up) የተሠራበት ዘመን ከ1998 እስከ 2004 የሆነ አንድ መኪና መዝግበው ሲልኩልን በተሸከርካሪ 28 (ሃያ ስምንት) ብር፣ የሥሪት ዘመኑ ከ2005 እስከ 2015 የሆነ ፒክ አፕ 33 (ሰላሳ ሦስት) ብር፣ እና ከ2016 በላይ ለሆነ 40 (አርባ) ብር እንዲሁም ለላንድ ክሮዘር (Land Cruiser) የተሠራበት ዘመን ከ1990 እስከ 1997 የሆነ መኪና መዝግበው ሲልኩልን በተሸከርካሪ 30 (ሰላሳ) ብር ፣ የሥሪት ዘመኑ ከ1998 እስከ 2007 የሆነ 35 (ሰላሳ አምስት) ብር፣ እና ከ2008 በላይ ለሆነ 45 (አርባ አምስት) ብር እንከፍላለን፡፡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተሸከርካሪ አይመዘገቡም፡፡ ሲጠቃለል የሥሪት ዘመናቸው ከ1990 እስከ 2022 የሆነ ለግል ሆነ ለመንግሥት መ/ቤቶች ለማንኛውም የኪራይ አገልግሎት ሊከራይ የሚችል በተለምዶ ማርክ ቱ እየተባለ የሚጠራውን መኪና ጨምሮ ማንኛውም ላንድ ክሮዘር እና ፒክ አፕ መኪኖችን በመመሪያው መሰረት መመዝገብ ይቻላል፡፡ ከመመሪያ ውጭ ለተመዘገበ ተሸከርካሪ እንዲሁም ስለተሸከርካሪው ባለንብረት አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር ወዘተ የተሳሳተ መረጃ መላክ ክፍያ አያስገኝም፡፡
መመሪያው ጸንቶ ስለሚቆይበት ጊዜ?
ይህ መመሪያ በመኪና ኪራይ ዶትኮም - በሚመለከተው ክፍል ተፈርሞ ከጸደቀበት ከዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ከዚህ ገጽ ላይ የተካተተውን መመሪያ ማሻሻል ሲያስፈልግ ከዚሁ ገጽ ላይ 7 የሥራ ቀናት ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የማንኛውንም አካል ፈቃድ ሳያስፈልግ መኪና ኪራይ ዶትኮም ይህን የሌሎችን ተሸከርካሪዎች መዝግቦ የመላክ መመሪያ በማንኛውም ጊዜ ሊያሻሽል ይችላል፡፡ መልካም እድል! ተሸከርካሪ ኪራይ ክፍል mekinakiray.com

የተሸከርካሪው ባለቤት መመዝገቢያ ቅጽ/ፎርም

የባለቤት ሙሉ ስም
የባለቤት ሙሉ ስም
ስም
የአባት ስም

የተሽከርካሪ መረጃ

Maximum upload size: 30MB

ይህን ቅጽ የሞላው ሰው ሙሉ ስም

ስም
ስም
የእርስዎ ስም
የአባት ስም
Maximum upload size: 516MB